አስቴር ተፈራ የተባሉት የነቀምት ከተማ ነዋሪ በወለጋ ዩኒቨርስቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አምስት ህጻናትን በሰላም መገላገላቸዉ ተገለጿል፡፡
ወ/ሮ አስቴር ተፈራ በአንድ ጊዜ 3 ወንዶችና 2 ሴት ልጆችን በሰላም መገላገላቸዉን ሆስፒታሉ አስታዉቋል፡፡

እናትዬዉን ጨምሮ ሁሉም ህጻናት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡ ወ/ሮ አስቴር ተፈራ ከአምስት አመታት በፊት አንዲት ሴት ልጅ መዉለዳቸዉም ተነግሯል፡፡