የመስቀል በዓል የኦሮሞ ህዝብ በጋራ የሚያከብረው የአብሮነት እና የመልካም ምኞቱን የሚገልጽበት መሆኑን በአደስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኦሮሞ ባህል እና ስነፅሁፍ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት አሰፋ ተፈራ (ዶ/ር) ገለፁ።
የመስቀል በዓል በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ፣ ዳመራ በመባል እንደሚከበር በማመላከት ይህም ህዝቡ ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር በአንድነት፣ በአብሮነት የመኖር ማሳያ እና የማንነት እሴት መገለጫው መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የኦሮሞ ህዝብ ለሀገር እድገት እና ብልጽግና ያለውን የዎል ምኞት የሚገልፅበት ነው ሲሉ ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።

የመስቀል ወይም የደመራ በዓል ማለት፣ በጋራ በመሆን አሮጌውን ዓመት አልፈን አዲስ እና የተስፋ ብርሀን ወዳለው ዓመት የምንሻገርበት የአዲስ አመት ተስፋን የምንሰንቅበትበት እንደሆነም ገልፀዋል ።
የዳመራ በዓል በማህበረሰቡ ዘንድ የሚከበረው ልክ እንደ ደመራው ብርሀን ሁሉ አሉታዊ አስተሳሰብን በአውታዊ አመለካከት በማብራት እሳቤ ደመራውን በመደመር ለኢሬቻ ክብረ በዓል ዝግጅት የሚያደርግበት መሆኑን አመላክተዋል።
በዚህ በመስቀል ዳመራ በዓል የ ኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች የህብረተሰቡ ክፍሎች ጋር በጋራ በመሆን የባህል ምግቦችን በመመገብ፣ አልባሳትን በመልበስ ወደ ውጭ ወጥቶ ፈጣሪውን በማመስገን፣ በደስታ ያሚያከብረው ትልቅ በዓል ነው ብለዋል።
በቀጣይም በዓሉ የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ብሔሮች ጋር ያለውን አብሮነት በተሻለ በሚገልጽበት እና በሚያሳድግበት መንገድ እንዲከበር ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በደራርቱ ተሬሳ