በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ተገለጸ
  • Post category:ወክታዊ

AMN መስከረም 15/ 2018 ዓ/ም

መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የ2018 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም እንዲከበር የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወቅ ሲሆን ነገ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4:00 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

በዚህም መሠረት፦

• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ፣

• ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች

ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፣

• ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ፣

• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር)፣

• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት፣

• ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፣

• ከራስ ሆቴል ወደ ስታድየም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል፣

• ከሐራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት፣

• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ፣

• ከዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ፣ እንዲሁም

• ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ከነገ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ መንገድ የሚዘጋ ሲሆን በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረዥም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን በመጠቀምና የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚያሳይዋቸው መንገድ በመጓዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

በዓሉ ያለ አንዳች የፀጥታ ስጋት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን ያስታወሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር እና የበዓሉ ታዳሚዎች ሠላምና ደህንነት እንዲጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጿል።

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪዉን አስተላልፏል፡፡

#አዲስሚዲያኔትዎርክ

#መስቀልደመራ

#addisababa

#Ethiopia

#Meskel

#celebrity

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review