ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጋር በሁለትዮሽና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸዉን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ከአለም አቀፍ የአቶሚክ ፎረም ጎን ለጎን ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጋር በሁለትዮሽና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የግብርና ሜካናይዜሽንን ጨምሮ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ በጋራ የምንሰራበት ሁኔታን ተመልክተናል ብለዋል፡፡