የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በተገኙበት የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በመከበር ላይ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የ2018 ዓ.ም የደመራ በዓልን በጸሎት በይፋ ከፍተዋል።
በበዓሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የፌደራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የእምነቱ ተከታዮች እና ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ጎብኚዎች ታድመዋል፡፡