የመስቀል ደመራ በዓል ህብረ ብሄራዊ አንድነታችንን የሚያሳይ ድንቅ በዓል መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ገልፀዋል፡፡
የ2018 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ በድምቀት ተከብሯል፡፡
በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት ሚኒስትሯ፤ ኢትዮጵያ እንደ ችቦ እንጨት በአንድ ላይ የተጋመዱ እና የተሳሰሩ በርካታ ባህሎች፣ እምነቶች፣ ውብ እሴቶችና ታሪኮች ያሏት ሀገር ናት ብለዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገበው ዓለም አቀፍ ሀብታችን የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል፤ ከእነዚህ እሴቶቿ መካከል አንዱ ነው ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡
የመስቀል ደመራ በዓል ህብረ ብሄራዊ አንድነታችንን የሚያሳይ፣ በትውልድ ቅብብሎሽ የዳበረና የጎለበተ ድንቅ በዓል መሆኑንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡
ንግስት ኢሌኒ መስቀሉን ለማግኘት ብዙ ለፍታለች፣ ደክማለችም፤ በመጨረሻ ግን ውጤት አግኝታለች ያሉት ሚኒስትሯ፣ የሀገራችንን ብልፅግና ለማስቀጠል የብዙዎችን ጥረት፤ ድካም እና አንድነት ይጠይቃል ብለዋል፡፡
በአስማረ መኮንን