የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጠናቀቅ ክስተት ለሃገራችን ዳግም ልደትን ያበሰረ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ተናገሩ

You are currently viewing የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጠናቀቅ ክስተት ለሃገራችን ዳግም ልደትን ያበሰረ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ተናገሩ

AMN – መስከረም 16/2018 ዓ.ም

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጠናቀቅ ክስተት ለሃገራችን ዳግም ልደትን ያበሰረ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ተናግረዋል፡፡

ፓትሪያሪኩ የ2018 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ በመስቀል አደባባይ ባስተላለፉት መልእክት፤ የዘንድሮው የመስቀል በዓል አከባበር ልዩ የሚያደርገው እግዚአብሄር የሰጠንን የውሃ ፀጋችንን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም በአንድነት ተባብረን ባካሄድነው ፅናት የህዳሴ ግድባችንን አጠናቀን ባስመረቅንበት ማግስት እየተከበረ መሆኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በግድቡ ግንባታ ታሪካዊ አሻራቸውን ያሳረፉ ፉሉ ምስጋና ይገባቸዋል አናመሰግናቸዋለንም ሲሉ ምስጋናቸውን በአደባባይ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ ሃገራችን ልትሰራቸው ያቀደቻቸው የልማት ስራዎችም በጥራት ተሰርተው ለህዝቡ ጥቅም እንዲውሉ ሁላችንም መረባረብ ይኖርብናል ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ታላላቅ እና ዘመን ተሻጋሪ አንዲሁም ችግርን አስወጋጅ የሆኑ ስራዎች እውን የሚሆኑት ህዝቡ በአንድነትና በህብረት ወደ ትግበራ ሲገባ ነው ያሉት ብፁዕ አቡነ ማትያስ፤ ለዚህም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምሳሌ ነው ብለዋል፡፡

ስለሆነም በህዳሴ ግድብ ያሳየነውን ትብብር እና ተነሳሽነት አጠናክረን ማስቀጠል ይገባል ሲሉ አባታዊ ምክራቸውንና መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በያለው ጌታነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review