• ግድቡ ሃይል ብቻ ሳይሆን ማሳካት መቻልንም ጭምር ማመንጨት የቻለ እንደሆነ ተጠቁሟል
“ይህ ግድብ እንዲገነባ ማንም አልፈለገም ነበር፡፡ ማንም የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ አልነበረም። በርካታ የፖለቲካና ሌሎች ችግሮችም ነበሩ፤ ቀላል መፍትሔዎች አልነበሩም። ኢትዮጵያውያን ፈተናዎችን የሚፈሩ አይደሉም፡፡ ፅኑ ናቸው፡፡ ተገዳዳሪ ወይም ጠላት ሲያጋጥማቸው አቅማቸውን በእጥፍ በማሳደግ ማሸነፍ ይችሉበታል… ኢትዮጵያ ይህንን ግድብ የገነባችው ሁሉንም ፈተናዎች በማሸነፍ ነው፡፡”
ይህንን የተናገሩት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተመረቀበት ወቅት መልእክት ያስተላለፉት የዊቢዩልድ ግሩም (ሳሊኒ ኮንስትራክሽን) ዋና ስራ አስፈፃሚ ፔይትሮ ሳሊኒ ናቸው፡፡ አዎ! እሳቸው እንደገለፁት ግድቡ በግንባታው ሂደት በፋይናንስ፣ በዲፕሎማሲ፣ በፀጥታና ደህንነትና በሌሎችም ጉዳዮች እልህ አስጨራሽ ፈተናዎችን አልፎ ነው እውን የሆነው፡፡ በርካታ ፈተናዎችን አልፎ ከዳር መድረሱ እንደ ግለሰብ፣ ማህበረሰብና እንደ ሀገር የሚያስተምረው ቁም ነገር ብዙ ነው፡፡
ዋና ሳጂን ገነት መልኬ የአዲስ አበባ ነዋሪ ናቸው፡፡ “ግድቡ የሁላችንንም ስሜት አንድ ያደረገ እና የኮረኮረ ነው። የተለያዩ የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን አልፎ ለመመረቅ የበቃ የአንድነታችን ድልድይ ነው፡፡ ከህፃን እስከ አዋቂ በነቂስ የተሳተፉበት የላብ ጠብታ ጭምር ነው” ሲሉ ለፍፃሜ መብቃቱ እንዳስደሰታቸው ነግረውናል፡፡
የህዳሴው ግድብ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ መጠናቀቅ መቻሉ የኢትዮጵያውያንን የይቻላል መንፈስን እና ቁርጠኝነትን ያሳያል ያሉት ዋና ሳጂን ገነት፤ የሰው ልጅም በህይወት ሲኖር በዚህ ዓለም ላይ እስካለ ድረስ ፈተናዎች እንደሚገጥመውና ማለፍም እንደሚችል ግድቡ ማሳያ መሆኑን ያነሳሉ፡፡
“እኔ እቅዶቼ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳኩ ሲቀሩ ተስፋ ቆርጬ አውቃለሁ። ነገር ግን ግድቡ ያለፈበትን ሂደት ስመለከት በቶሎ መሰበሬ ይቆጨኛል። ከዚህ በኋላ በህይወቴ ላሳካው የምፈልገውን ህልም እንዴት ማለፍ እንዳለብኝ ጥንካሬና ብርታት ሆኖኛል። ችግሮች እንደሚያልፉ፤ ተስፋ ማድረግ እንደሚያሻግር ግድቡ ህያው ምሳሌዬ ነው” ይላሉ ዋና ሳጅን ገነት፡፡
ፈተናዎች እንደሚያጠነክሩ፣ የወደቀ እንደሚነሳ፣ አይደርስም የተባለ እንደሚደርስ እንዲሁም የማልችለውና የማላልፈው ምንም ነገር እንደሌለ ከግድቡ ትምህርት አግኝቻለሁ፡፡ በቤተሰብ ውስጥ እናት፣ አባት እና ልጆች በአንድ ጎጆ ሲኖሩ መተባበር እና በአንድ መስራት እንዲሁም መረዳዳት ወሳኝ መሆኑን እንዲሁ ሲሉ አክለዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሀገራችንን ስም በበጎ ያስጠራ በመሆኑ ደስተኛ ነኝ ሲሉ የገለፁልን ደግሞ ሌላኛዋ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ ላቀች ሃይሌ ናቸው። “የህዳሴ ግድብ አይችሉም የተባልነውን ወደ መቻል የቀየርንበት፣ ዓድዋን መልሰን የደገምንበት፣ የአፍሪካ ተምሳሌት የሆንበት እንዲሁም ዓለምን ያስደመምንበት፤ ‘ዓባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል’ የሚለውን ብሂል የሻርንበት ነው” ብለዋል።
ግድቡ ለመመረቅ ብዙ ችግሮችን እንዳለፈ ሁሉ፤ እኛም በህይወታችን ብዙ ዓይነት ችግሮች በዕለት ተዕለት ህይወታችን ይገጥሙናል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ችግሮችን አግዝፈን በማየት ተስፋ እንቆርጣለን፡፡ የህዳሴ ግድብ በህይወታችን ‘አይቻልም’ ብለን ያቆምናቸው ነገሮች እንዲቆጩን እና ለችግሮች እጅ መስጠት እንደሌለብን ያስተምረናል፡፡ ግድቡ ከመገንባቱ አስቀድሞና በግንባታው ሂደት ያጋጠሙ ፈተናዎችን አልፎ መመረቁ በቁርጠኝነትና በጋራ ከተሰራ ምንም የማይቻል ነገር እንደሌለ ማሳያ እንደሆነ ወይዘሮ ላቀች ይናገራሉ፡፡
“እኔ ከዓባይ የተማርኩት በፅናት፣ በአንድነት፣ በትግል ራሴን ማበርታት፣ ቀን ከሌት በመስራት ራሴን መለወጥ እንዳለብኝ ነው። ግድቡ እንደተጠናቀቀው ሁሉ በህይወታችን የምንጀምራቸው ነገሮችም መጨረሻ እንዳላቸውና ተስፋ መቁረጥ እንደሌለብኝ የተረዳሁበት ነው” ሲሉ ለወደፊት የይቻላልን መንፈስ ይዘው የህይወት ውጣ ውረዶችን ማለፍ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
አቶ ደሳለኝ ካሴ በበኩላቸው፣ በዓባይ ውሃ ላይ ልማት ማካሄድ ለዘመናት የማይቻል ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡ ለሀገሩ ባዕዳና እንግዳ፤ ለሌሎች ሀገራት ብቻ ሲሳይ ነበር፡፡ ወንዙ ላይ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን መገንባት መቻሉ እንደ ግለሰብ ተስፋ አለመቁረጥን፣ ‘ይሳካል’ የሚል መንፈሰ ጠንካራነትን፣ ከተናጠል ይልቅ በጋራ መስራትን፣ የአንድነትን ሃይል እንዲሁም የአላማ ፅናትን እንደተማሩበት ነግረውናል፡፡
ከላይ እንደተጠቀሰው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተጀመረበት ብሎም ለፍጻሚ የደረሰበት መንገድ በግለሰብ ደረጃ ብዙ የሚያስተምር ነው፡፡ የዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸው የስነ ልቦና ባለሙያም ይኸንኑ ሀሳብ የሚያጠናክር አስተያየት ሰጥተዋል።
የስነ ልቦና ባለሙያ የሆኑት ልዑልሰገድ በየነ (ዶክተር) እንደገለጹት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለምርቃት እስኪበቃ ድረስ ያለፈበት ውጣ ውረድ ሰዎች ለሚኖሩት የዕለት ተዕለት ኑሮ ብዙ የሚሰጠው ትምህርት እንዳለ ያብራራሉ። ማንኛውም ሰው እቅድ አቅዶ ወደ ስራ ሲገባ ሊያሳካው የሚችለው መሆኑን፤ ሊያውቀውና ሊረዳው ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ የተፈጠረው ለቁጥር እንጂ ለስኬትና ለልማት አይደለም ወደሚል ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ይገባል፡፡
ህልም እንዲሳካ ከሚያደርጉ መሳሪያዎች ውስጥ የመጀመሪያው አንድ ሰው ሊያሳካ ያሰበውን ነገር ወደ ውስጡ ዘልቆ መግባቱን እና ለራሱ፣ ለቤተሰቡና ለሀገሩ ጠቃሚ መሆኑን ማረጋገጥ፣ እቅዶቹ ችግሮች ቢገጥሙት እንኳን መቋቋም የሚችል ህልም ያለው መሆን እንዲሁም ከጥሪው እና ከጥንካሬው ጋር የሚስማማ ማድረግ እንደሚገባው ይናገራሉ፡፡
ባለሙያው በማብራሪያቸው፣ “እቅዳችንን አቅደን ወደ ህልማችን ለመድረስ ስንነሳ እንዳይሳካ የሚያደርጉ የተለያዩ ውጣ ውረዶችና ተግዳሮቶች ማጋጠሙን ልንወደው ይገባል፡፡ አዋጭ ናቸው። ለእኛ ተግዳሮቶች ቢመስሉንም እንድናሳካ የሚረዱን ሽልማቶች ናቸው። ምክንያቱም ዋጋ ካልከፈልን ሽልማት አናገኝምና” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የሰው ልጅ ማሳካት የማይችለው ነገር እንደሌለ ማሳያ የሆነውንና በብዙ ውጣ ውረድ ያለፈውን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ያነሱት የስነ ልቦና ባለሙያው፤ አንዳንድ ኢትዮጵያውያንም ሆኑ የዓለም ሀገራት እንደማይሳካ ተስማምተውበት የነበረ ቢሆንም በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ትብብር እውን ሆኖ ተመርቋል፡፡
ለዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ያሉትን ምሁሩ ሲያብራሩ፣ “የኢትዮጵያ ህዝብ ወደራሱ ተመልሶ፣ ይሳካል ብሎ ማመኑ እና ለሀገራችን ብሎም ለአፍሪካ ይጠቅማል የሚል ርዕይ መሰነቁ ነው፡፡ ይህም ማንኛውም ልናሳካው የፈለግነው እቅድ ከአቅማችን በታች እንጂ በላይ እንዳልሆነ ያረጋገጥንበት ነው” ብለዋል፡፡
እንደ ባለሙያው ገለጻ፣ የግድብ ግንባታውን ስንጀምር ከርዕይ ጀምረን ተግዳሮቶችን እንደ መወጣጫ መሰላል በመጠቀም “ካላጠናቀቅን አንቆምም” የሚል ቁርጠኛ አቋም የያዝን አመራሮችና ኢትዮጵያውያን ስለነበርን አሳክተን በተግባር አሳይተናል፡፡ በግድቡ የተለያየ የፖለቲካ አቋምና አመለካከት ያላቸው አካላት በአንድነት በመቆም ‘እንኳን ደስ አለን’ እያሉ ደስታቸውን ሲገልፁም ታይተዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ግድቡ ሃይልን ብቻም ሳይሆን መስማማትንም፣ አንድነትን፣ ማሳካት መቻልንም ጭምር ማመንጨት መቻሉን ነው፡፡
ይህን ትልቅ የህዳሴ ግድብ ስኬት ወደ እያንዳንዱ ሰው ህይወት በማምጣት ያለፈበት ውጣ ውረድና ስኬት የግል ህዳሴን መገንባት የሚያስችል መሆኑን የገለፁት ልዑልሰገድ (ዶ/ር)፣. ይህም ሲባል ግብ አስቀምጠን፣ ጠንካራ ጎናችንንና ጥሪያችንን እንደ መሳሪያ በመጠቀም፣ ደካማ ጎናችንን በማወቅ፣ ስልታዊ አብሮ መስራትን መጠቀም ህልምን ማሳካትና ወደፈለጉበት ደረጃ እንዲደርሱ ያደርጋል፡፡
የህዳሴው ግድብ ውጣ ውረዶችን አልፎ ለመመረቅና ጥቅም ላይ ለመዋል እንደበቃው ሁሉ፤ የሰው ልጆችም ለሚኖሩት የግል ህይወት ውጣ ውረዶች ሊያጋጥሙት እንደሚችሉ እና ተግዳሮቶችን እንደ መሰላል በመጠቀም እንደሚያሳኩት ማሳያ መሆኑን ነው የስነ ልቦና ባለሙያው የተናገሩት፡፡

ዋና ሳጂን ገነት መልኬ የአዲስ አበባ ነዋሪ ናቸው፡፡ “ግድቡ የሁላችንንም ስሜት አንድ ያደረገ እና የኮረኮረ ነው፡፡ የተለያዩ የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን አልፎ ለመመረቅ የበቃ የአንድነታችን ድልድይ ነው፡፡ ከህፃን እስከ አዋቂ በነቂስ የተሳተፉበት የላብ ጠብታ ጭምር ነው” ሲሉ ለፍፃሜ መብቃቱ እንዳስደሰታቸው ነግረውናል፡፡
የህዳሴው ግድብ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ መጠናቀቅ መቻሉ የኢትዮጵያውያንን የይቻላል መንፈስን እና ቁርጠኝነትን ያሳያል ያሉት ዋና ሳጂን ገነት፤ የሰው ልጅም በህይወት ሲኖር በዚህ ዓለም ላይ እስካለ ድረስ ፈተናዎች እንደሚገጥመውና ማለፍም እንደሚችል ግድቡ ማሳያ መሆኑን ያነሳሉ፡፡
“እኔ እቅዶቼ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳኩ ሲቀሩ ተስፋ ቆርጬ አውቃለሁ። ነገር ግን ግድቡ ያለፈበትን ሂደት ስመለከት በቶሎ መሰበሬ ይቆጨኛል። ከዚህ በኋላ በህይወቴ ላሳካው የምፈልገውን ህልም እንዴት ማለፍ እንዳለብኝ ጥንካሬና ብርታት ሆኖኛል። ችግሮች እንደሚያልፉ፤ ተስፋ ማድረግ እንደሚያሻግር ግድቡ ህያው ምሳሌዬ ነው” ይላሉ ዋና ሳጅን ገነት፡፡
ፈተናዎች እንደሚያጠነክሩ፣ የወደቀ እንደሚነሳ፣ አይደርስም የተባለ እንደሚደርስ እንዲሁም የማልችለውና የማላልፈው ምንም ነገር እንደሌለ ከግድቡ ትምህርት አግኝቻለሁ፡፡ በቤተሰብ ውስጥ እናት፣ አባት እና ልጆች በአንድ ጎጆ ሲኖሩ መተባበር እና በአንድ መስራት እንዲሁም መረዳዳት ወሳኝ መሆኑን እንዲሁ ሲሉ አክለዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሀገራችንን ስም በበጎ ያስጠራ በመሆኑ ደስተኛ ነኝ ሲሉ የገለፁልን ደግሞ ሌላኛዋ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ ላቀች ሃይሌ ናቸው፡፡ “የህዳሴ ግድብ አይችሉም የተባልነውን ወደ መቻል የቀየርንበት፣ ዓድዋን መልሰን የደገምንበት፣ የአፍሪካ ተምሳሌት የሆንበት እንዲሁም ዓለምን ያስደመምንበት፤ ‘ዓባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል’ የሚለውን ብሂል የሻርንበት ነው” ብለዋል፡፡
ግድቡ ለመመረቅ ብዙ ችግሮችን እንዳለፈ ሁሉ፤ እኛም በህይወታችን ብዙ ዓይነት ችግሮች በዕለት ተዕለት ህይወታችን ይገጥሙናል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ችግሮችን አግዝፈን በማየት ተስፋ እንቆርጣለን፡፡ የህዳሴ ግድብ በህይወታችን ‘አይቻልም’ ብለን ያቆምናቸው ነገሮች እንዲቆጩን እና ለችግሮች እጅ መስጠት እንደሌለብን ያስተምረናል፡፡ ግድቡ ከመገንባቱ “ይህ ግድብ እንዲገነባ ማንም አልፈለገም ነበር፡፡ ማንም የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ አልነበረም። በርካታ የፖለቲካና ሌሎች ችግሮችም ነበሩ፤ ቀላል መፍትሔዎች አልነበሩም። ኢትዮጵያውያን ፈተናዎችን የሚፈሩ አይደሉም፡፡ ፅኑ ናቸው፡፡ ተገዳዳሪ ወይም ጠላት ሲያጋጥማቸው አቅማቸውን በእጥፍ በማሳደግ ማሸነፍ ይችሉበታል… ኢትዮጵያ ይህንን ግድብ የገነባችው ሁሉንም ፈተናዎች በማሸነፍ ነው፡፡”

በፋንታነሽ ተፈራ