ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአይነቱ የመጀመሪያ እና እጅግ ዘመናዊ የሆነዉ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ተመርቆ ስራ መጀመሩን ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአይነቱ የመጀመሪያ እና እጅግ ዘመናዊ የሆነዉ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ተመርቆ ስራ መጀመሩን ገለጹ

AMN መስከረም 18/2018

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአይነቱ የመጀመሪያ እና እጅግ ዘመናዊ የሆነዉን የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስን መርቀን ስራ አስጀምረናል ብለዋል።

የከተማችን አስተዳደር በሚሰራቸዉ የልማት ስራዎች ሁሉ ኪነ ጥበብን አበይት የትኩረት አቅጣጫዉ አድርጎ እየተገበረ ይገኛል።

በዚህም ባለፉት ጥቂት አመታት ነባሮቹን በማደስ እና ዘመናዊ እና ደረጃቸዉን የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ እንዲሁም አዳዲስ እና ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸዉ የቲያትርና የሲኒማ ኮምፕሌክሶች ገንብተን ለኪነ ጥበብ ዘርፉ እድገት አስተዋፆ እያበረከትን እንገኛለን ብለዋል።

ዛሬ ያስመረቅነዉ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ፦

ባለ14 ወለል ህንፃ ፣2 ዘመናዊ ሲኒማ ቤቶችን

፣የቲያትር አዳራሽ ፣ 3 የተለያዩ አዳራሾችን ፣ የሆቴል እና ሪስቶ ራት ዘመናዊ ካፍቴሪያዎችን እና ፓርኪንግ አገልግሎት ይዟል ።

የጥበብ ስራ በአዳራሽ ብቻ የተወሰነ ባለመሆኑ እና ወደ ማህበረሰቡ ቀረብ እንዲል በከተማችን በተገበርነዉ ሁለንተናዊ ለዉጥ የተለያዩ የዉጭ የኪነ ጥበብ ስራ የሚከወንባቸዉ ከ 160 በላይ አንፊ ቲአትርና ፕላዛዎችን ገንብተን ለአገልግሎት አዉለናል ሲሉ ገልጸዋል።

የኪነ ጥበብ ዘርፉ በፈጠረዉ ምቹ ሁኔታ የዉስጥ ቁጭትን በመፍጠር ትዉልድን በመልካም ስራ እንድናንፅ ከወዲሁ ጥሪዬን አቀርባለዉ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review