ስለ ገዳ ስርአት፣ ስለ አፋን ኦሮሞና ሌሎች በኦሮሞ ህዝብ ፍልስፍና ላይ ትኩረት ያደረጉ መፃህፍት ተመረቁ

You are currently viewing ስለ ገዳ ስርአት፣ ስለ አፋን ኦሮሞና ሌሎች በኦሮሞ ህዝብ ፍልስፍና ላይ ትኩረት ያደረጉ መፃህፍት ተመረቁ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN – መስከረም 18/2018 ዓ.ም

የኦሮሞ ምርምር ማህበር ያሳተማቸውን መጽሐፎች የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እያስመረቀ ይገኛል።

መጽሐፍቶቹ በዋናነት በሐገር ውስጥና በውጪ ሐገር ቋንቋ የተዘጋጁ ሲሆን በዋናነት ስለ ገዳ ስርአት፣ ስለ አፋን ኦሮሞና ሌሎች በኦሮሞ ህዝብ ፍልስፍና ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው ተብሏል።

መጽሐፍቱ በተለይ ጥራት ያለው ትምህርትና ሳይንስንና ምርምርን በማሳደግ ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመድረኩ ተናግረዋል።

የኦሮሞ ምርምር ማህበርም በአሁን መንግስት አሰራርም ሆነ በትውልድ ውስጥ የሚታዩ ህፀጾችን ነቅሶ በማውጣት፣ እንዲታረሙ በማድረግ ብሎም ለቀጣይም አቅጣጫን በመጠቆም አሰወተዋጽኦው የጎላ ነው ብለዋል።

አቶ ሽመልስ አክለውም እንደ መንግስት ተቋሙ የተቋቋመለትን አላማ እንዲያሳካ የመደገፍ ስራ ይሰራል ብለዋል።

በመድረኩ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ እድገት፣ በኦሮሞ ህዝብ ታሪክ እንዲሁም ትግል ውስጥ ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሼክ በክሪ ሳጰሎ እና ኃይሌ ፊዳ (ዶ/ር) እውቅና ተሠጥቷል።

በሄኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review