ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የክልሉን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ሥራ አስጀመሩ

You are currently viewing ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የክልሉን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ሥራ አስጀመሩ

AMN መስከረም 18/2018 ዓ.ም

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የክልሉን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

የአማራ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ክልላዊ የሥራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

‎እየተከናወነ ባለው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የምረቃና የሥራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

‎በተጨማሪም በክልሉ የሚገኙ ተቋማት ሃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች እንዲሁም የህብረተሰብ ተወካዮች መታደማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

‎መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንደ ሀገር ጊዜና ጉልበትን ለመቆጠብ እንዲሁም ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ መሆኑ ይታወቃል።

አገልግሎቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመኑን የሚመጥን አሰራር በመዘርጋት በአንድ ቦታ ላይ ፈጣን፣ ግልጽና ተአማኒነት ያላቸው የተለያዩ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ለመስጠት ያለመ ነው።

ይህም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያየዘ ህብረተሰቡ ሲያነሳቸው የነበሩ ቅሬታዎችን በመፍታት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ፋይዳው የጎላ መሆኑም ተገልጿል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review