በካይ የፍሳሽ ቆሻሻን በመልቀቅ ከጥፋቱ መታረም ያልቻለዉ ድርጅት በድጋሚ ደንብ ተላልፎ በመገኘቱ 800 ሺህ ብር መቀጣቱ ተገለጸ

You are currently viewing በካይ የፍሳሽ ቆሻሻን በመልቀቅ ከጥፋቱ መታረም ያልቻለዉ ድርጅት በድጋሚ ደንብ ተላልፎ በመገኘቱ 800 ሺህ ብር መቀጣቱ ተገለጸ

AMN መስከረም 19/2018

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ስሙ ቦቼ ሰፈር አካባቢ በኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ ስር የሚገኘዉ አዋሽ የቆዳ ፋብሪካ ድርጅት ከፋብሪካው የመነጨ በካይ የፍሳሽ ቆሻሻን ወደ ወንዝ በመልቀቁ 800 ሺህ ብር መቀጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ገለፀ።

ድርጅቱ ከዚህ በፊት ተመሳሳይ የደንብ መተላለፍ ፈጽሞ በመገኘቱ 400 ሺህ ብር መቀጣቱን ባለስልጣኑ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል።

ተቋሙ ከጥፋቱ ሳይታረም ያመነጨውን በካይ ፈሳሽ ቆሻሻን በድጋሚ ጨለማን ተገን አድርጎ ወደ ወንዝ ሲለቅ ለባለስልጣኑ በደረሰዉ የማህበረሰብ ጥቆማ መሰረት በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ በተቀመጠው የቅጣት አወሳሰድ እርምጃ በተደጋጋሚ ጥፋት አጥፊ ሆኖ በመገኘቱ 800 ሺህ ብር ተቀጥቷል።

የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት መድቦ የወንዝ ዳርቻ የልማት ስራዎችን እየሰራ ባለበት ወቅት እንደዚህ አይነት ተግባር መፈፀም ተገቢ አለመሆኑን የገለጸዉ ባለስልጣኑ ሌሎች ተቋማትም ሆኑ ግለሰቦች ከዚህ እርምጃ መማር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review