በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ “ኢሬቻ ግራንድ ኮንሰርት” መስከረም 23 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ኑማን ኢቨንትና ኘሮሞሽን ድርጅት አስታውቋል፡፡
ኮንሰርቱ ከመዝናኛነት ባለፈ የኦሮሞ ባህልን ማስተዋወቅ፤ እንዲሁም አብሮነትን እና ትብብርን ያነገቡ መልዕክቶች የሚተላለፍበት መሆኑን አዘጋጅ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
ኮንሰርቱን በማስመልከት በራማዳን ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ኮንሰርቱ ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዕለቱ አርቲስት ጃምቦ ጆቴ፣ ጉቱ አበራ፣ ሹኩሪ ጀማል፣ አዳም መሀመድ፣ ሌንጮ ገመቹን ጨምሮ አስር እውቅ እና ዝነኛ አርቲስቶች በመድረኩ ሥራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።
ኢሬቻ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና የአንድነት በዓል በመሆኑ ኮንሰርቱም ይህን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተለያዩ የኪነ ጥበብ ስራዎች ይቀርቡበታል ተብሏል።
የዘንድሮው አመት የኢሬቻ በአል “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት“ በሚል መሪ ቃል በድምቀት ይከበራል።
በ-ታምሩ ደምሴ