በታላላቅ ውድድሮች ላይ ተሳትፋ ለሃገሯ ሜዳልያ ማምጣት እንደምትፈልግ ብስክሌተኛ ፅጌ ካህሳይ ገለፀች

You are currently viewing በታላላቅ ውድድሮች ላይ ተሳትፋ ለሃገሯ ሜዳልያ ማምጣት እንደምትፈልግ ብስክሌተኛ ፅጌ ካህሳይ ገለፀች

AMN-መስከረም 20/2018 ዓ.ም

በቅርቡ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተደረገው 125ኛ የዓለም የብስክሌት ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያዊቷ ፅጌ ካህሳይ ትኩረት ስባለች፡፡ ወጣቷ ብስክሌተኛ በሁለት የውድድር ዓይነቶች ተሳትፋ ከአፍሪካ በቀዳሚነት አጠናቃለች፡፡

በወጣቶች የጎዳና ታይም ትሪያል ከዓለም 24ኛ ደረጃ ወጥታለች፡፡ 18.3 ኪሎ ሜትር በፈጀው በዚህ ውድድር ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆን ችላለች፡፡

ፈታኝ በሆነው ሌላ የጎዳና ላይ ውድድር የተሳተፈችው ፅጌ፤ በርካቶች ያልጠበቁትን ውጤት አምጥታለች፡፡

የመስፍን ኢንጅነሪንግ ክለብ አባል የሆነችው ብስክሌት ጋላቢዋ፤ 74 ኪሎ ሜትር የፈጀውን ውድድር ሰባተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡ በአፍሪካ ግን ቀዳሚነቱን ለማንም አላስነካችም፡፡

በዚህ ትልቅ ውድድር ላይ በመሳተፏ እንደተደሰተች የገለፀችው ፅጌ ከዚህ የበለጠ ውጤት ማስመዝገብ እንደምትፈልግ ከ ኤ ኤም ኤን ጋር በነበራት ቆይታ ተናግራለች፡፡

’’በታላላቅ ውድድሮች ላይ ተካፍዬ ለሀገሬ ሜዳልያዎችን ማምጣት እፈልጋለሁ፡፡ የብስክሌት ስፖርት በደንብ ከተሰራበት ጥሩ ውጤት ማምጣት ይቻላል’’ ስትል ገልፃለች፡፡

በበጀት እጥረት እንዲሁም በቪዛ እጦት በርካታ ጠቃሚ ውድድሮች እንዲሚያልፋቸው የጠቆመችው ፅጌ የሚመለከታቸው አካላት እገዛ እንዲያደርጉላቸው ጥሪዋን አቅርባለች፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review