የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ከ300 ነጥብ ወደ 297 ዝቅ መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

You are currently viewing የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ከ300 ነጥብ ወደ 297 ዝቅ መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

AMN – መስከረም 21/2018 ዓ.ም

ትምህርት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤትን ከ300 ወደ 297 ዝቅ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም ነጥባቸው ከ 300 በላይ ወይም በመቶኛ ከ 50 በመቶ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲቀላቀሉ ተደርጎ የቆየ ሲሆን፤ በተሸሻለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት መሰረት በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና አማካይ ውጤታቸው ከ 49.5 እስከ 49.99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ውጤታቸው ወደ 50 በመቶ እንዲጠጋጋ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዚህም ውሳኔ መሰረት፤ ውጤታቸው ከ297 በላይ ወይም በመቶኛ 49.5 በመቶ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች፤ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግባት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review