እንግሊዛዊ ማይክል ኦሊቨር የባርሴሎና እና ፒ ኤስ ጂን ጨዋታ እንዲመሩ ተመደቡ

You are currently viewing እንግሊዛዊ ማይክል ኦሊቨር የባርሴሎና እና ፒ ኤስ ጂን ጨዋታ እንዲመሩ ተመደቡ

AMN-መስከረም 21/2018 ዓ.ም

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ዛሬ ምሽት በስፔን ካታሎን ይደረጋል፡፡ ዘንድሮ ምንም ጨዋታ ያልተሸነፈው ባርሴሎና በሜዳው የባለፈው ዓመት ሻምፒዮኑን ፓሪሰን ዠርመንን ይጋብዛል፡፡

በቀድሞ ውጤታማ ዳኛ ሮቤርቶ ሮሴቲ የሚመራው የአውሮፓ እግር ኳስ ዳኞች ኮሚቴ ለምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ እንግሊዛዊውን ማይክል ኦሊቨር መድቧል፡፡ ከፈረንጆቹ 2012 ጀምሮ የፊፋ ባጅን የያዙት የ40 ዓመቱ ኦሊቨር የምሽቱን ጨዋታ ለመምራት ስፔን ገብተዋል፡፡

ማይክል ኦሊቨር በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ታላላቅ ደርቢዎችን ጨምሮ በርካታ ጨዋታዎችን መርተዋል፣ እየመሩም ነው፡፡ አልቢትሩ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ፣ አውሮፓ ዋንጫና የዓለም ዋንጫ በርካታ ጨዋታዎችን እንዳጫወቱም ይታወቃል፡፡

ስትዋርት በርትና ጄምስ ማይንዋሪንግ በረዳት ዳኝነት፣ አንድሪው ማድሊ በአራተኛ ዳኝነትና አርሰናልና ኒውካስትልን ያጫወቱት ጃሬድ ጊሌት በረዳት ምስል ዳኝነት (ቪ ኤ አር) ለምሽቱ ጨዋታ መመደባቸው ታውቋል፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review