ዓለም አቀፍ የከተማ ማውንቴን ባይክ ውድድር በአዲሰ አበባ ይካሄዳል

You are currently viewing ዓለም አቀፍ የከተማ ማውንቴን ባይክ ውድድር በአዲሰ አበባ ይካሄዳል

AMN-መስከረም 21/2018 ዓ.ም

በመጪው መጋቢት ወር ዓለም አቀፍ የከተማ ማውንቴን ባይክ ውድድር በአዲሰ አበባ ይደረጋል ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌደሬሽን ከአለም አቀፉ የብስክሌት ህብረት ዩ ሲ አይ (UCI) ጋር ባለው ግንኙነት በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከናውን የከተማ ውስጥ የብስክሌት ውድድር በአዲሰ አበባ እንደሚካሄድ ፌደሬሽኑ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡

ከአሜሪካና ከአውሮፓ የተውጣጡ 25 ሃገራት ይሳተፋሉ ተብሏል።

ስለውድድሩ ለመንግስት አሳውቀን አውቅና አግኝተናል ሲሉ የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌደሬሽን ፕሬዚዳናትና የአፍሪካ ብስክሌት ኮንፌደሬሽን ቦርድ አባል አቶ ወንድሙ ሃይሌ ገልፀዋል፡፡

ውድድሩ ከአለም አቀፉ ብስክሌት ህብረት እውቅና ማግኘቱ የተነገረ ሲሆን የዉድድር መርሃ ግብሩ የአዲስ አበባን የከተማ ልማትና እድገትን ለአለም ለማሳየት እድል እንዳለውም ተጠቅሷል፡፡

በዮናስ ሞላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review