የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለሦስት አዳዲስ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ፍቃድ ሰጠ

You are currently viewing የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለሦስት አዳዲስ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ፍቃድ ሰጠ

AMN – መስከረም 21/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሰፊ የፈቃድ ማመልከቻ ግምገማ ሂደት በኋላ ለሦስት አዳዲስ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ፍቃድ መስጠቱን አስታወቀ።

በዚህም በባለስልጣኑ ፈቃድ የተሰጣቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ቁጥር ከስምንት ወደ አስራ አንድ ከፍ ብሏል፡፡

አዳዲሶቹ ፈቃድ የተሰጣቸው አገልግሎት ሰጭዎች እና የፈቃድ አይነቶችም መካከል፡-

1.ፈርስት አዲስ ኢንቨስትመንት ባንክ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር – በኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ፣

2. ኢግናይት ካፒታል ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር – በሰነደ መዋዕለንዋይ ማማከር ዘርፍ፣

3. ዙሪ ካፒታል አክሲዮን ማህበር – በሰነደ መዋዕለንዋይ ማማከር ዘርፍ ናቸው።

በመርሐ-ግብሩም የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልቁ፣ በእለቱ ፈቃድ ለተሰጣቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ሀገራችን በጀመረችው አካታች እና ሁሉን አቀፍ የካፒታል ገበያ ስርዓት ግንባታ ላይ ወሳኝ ሚና እንዲጫወቱ አሳስበዋል፡፡

በዛሬው እለት ፈቃድ ከተሰጣቸው ሶስቱ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች መካከል ፈርስት አዲስ ኢንቨስትመንት ባንክ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከባንክ ግሩፕ ውጭ ፈቃድ የተሰጠው የመጀመሪያው ኢንቨስትመንት ባንክ ሆኗል፡፡

በወንድማገኝ አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review