የኢሬቻ በዓልን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን በኢትዮጵያዊ ቅን መስተንግዶ ከጅምሩ እስከ ፍፃሜ ለማገልገል መዘጋጀታቸውን የሰላምና ፀጥታ ሃይል አባላት ገልፀዋል።
የኢሬቻ በዓል በስኬት በድምቀት ለማክበር የሚያስችል የጋራ ጥምር የፀጥታ ኃይል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስምሪት የመስጠት መርሃግብር ተካሂዷል።
በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ታዳሚዎች የሚታደሙበት የኢሬቻ በዓል ዕሴቱን ጠብቆ በስኬት እንዲከበር ከሁሉም የተውጣጡ የፀጥታ ሃይሎች ስምሪት ተሰጥቷቸዋል።

በስምሪት መስጠት መርሃግብሩ የተገኙት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና፤ ኢሬቻ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በፍፁም ስኬት እንዲከበር በክፍለ ከተማው አስተማማኝ የፀጥታ ስምሪት መሰጠቱን ገልፀዋል፡፡
የፀጥታ አካላቱ በተሰጣቸው ስምሪት መሰረት ህብረተሰቡን እንዲያገለግሉም ዋና ስራ አስፈፃሚው አሳስበዋል።
የኢሬቻ በዓልን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን በኢትዮጵያዊ ቅን መስተንግዶ ከጅምሩ እስከ ፍፃሜ ለማገልገል መዘጋጀታቸውን የጥምር ፀጥታ ሀይል አባላቱ ለኤ.ኤም.ኤን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በ-ይታያል አጥናፉ