ስድስት ወሳኝ ተጫዋቾቹን በጉዳት ያጣው ፓሪሰን ዠርማ ባርሴሎናን አሸነፈ

You are currently viewing ስድስት ወሳኝ ተጫዋቾቹን በጉዳት ያጣው ፓሪሰን ዠርማ ባርሴሎናን አሸነፈ

AMN-መስከረም 22/2018 ዓ.ም

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ በጉጉት የተጠበቀው የባርሰሎና እና ፓሪሰን ዠርማ ጨዋታ በፈረንሳዩ ክለብ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በኢስታዲዮ ኦሎምፒኮ ሊውስ ካምፓኒ በተደረገው ጨዋታ ባርሳ ፌራን ቶሬስ ባስቆጠረው ግብ መምራት ቢችልም ውጤቱን አላስጠበቀም። ፒ ኤስ ጂ ሴኒ ማዩሉ እና ጎንካሎ ራሞስ ግቦች ሦስት ነጥቡን ወስዷል።

በሊውስ ኤነሪኬ የሚመራው ቡድን ባሎን ድ ኦር አሸናፊው ኡስማን ዴምቤሌን ጨምሮ ስድስት ወሳኝ ተጫዋቾቹን በጉዳት ምክንያት አልተጠቀመም።

በሌሎች ጨዋታዎች አርሰናል በጋብርኤል ማርቲኔሊ እና ቡካዮ ሳካ ግቦች ኦሎምፒያኮስን 2ለ0 ማሸነፍ ሲችል ፤ ማንችስተር ሲቲ ከሞናኮ 2ለ2 ተለያይቷል። ለሲቲ ኧርሊንግ ሃላንድ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ አሳርፏል። ናፖሊ በራስመስ ሆይሉንድ ሁለት ግቦች ታግዞ ስፖርቲንግ ሊዝበንን 2ለ1 አሸንፏል።

ቦሩሲያ ዶርትመንድ አትሌቲክ ቢልባኦን 4ለ1 ሲረታ ቪያሪያል ከ ጁቬንቱስ ጨዋታቸውን 2ለ2 አጠናቀዋል። ባየር ሊቨርኩሰን ከ ፒ ኤስ ቪ አይንዶቨን ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ መጠናቀቅ ችሏል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review