ኢሬቻ ከባህላዊ ትውፊቱ ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች አብረው የሚያከብሩት ኢሬቻ የአንድነት፣ የሰላም እና የወንድማማችነት ምልክት መሆኑን የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ተናግረዋል።
የዕድሜ ልዩነት ሳይፈጠር የኦሮሞ ሕዝብ የኢሬቻ በዓልን ለዘመናት በጋራ ሲያከብረው የቆየ በዓል መሆኑን ምክትል ቢሮ ኃላፊው አንስተዋል።
የፍቅርና የሰላም ተምሳሌት የሆነው ኢሬቻ በዓልን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባጠናቀቅንበት ወቅት መካሄዱ ልዩ ያደርገዋል ያሉት አቶ ዳዊት በዓሉ ከመላው ዓለም የሚመጡ ሰባት ሚሊየን የሚጠጉ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙበት አስረድተዋል።
የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት በልዩ ሁኔታ ለማክበር በጋራ እየተሰራ እንደሚገኝ የወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ አዱኛ ገልጸዋል። በዓሉን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን በፍቅር ማስተናገድ እንደሚገባም ወይዘሮ መቅደስ አመላክተዋል።
ኢሬቻን አስመልክቶ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ገለጻ ያደረጉት ወይዘሮ ስንት ነዋይ፤ የበዓሉ መከበር ዋና ዓላማ አገራዊ አንድነትን ለማጽናት እና ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን ለማጠናከር መሆኑን አስረድተዋል።
በዳዊት ተስፋዬ