ኢሬቻ ከተለያዩ አከባቢዎች የተወጣጡ ባህላዊ ትውፊቶችና እሴቶች የሚታዩበት መድረክ መሆኑ ተገለጸ

AMN – መስከረም 22/2018 ዓ.ም

በርካታ ህዝብ የሚገኝበት የኢሬቻ በዓል የተለያዩ አልባሳት፣ ጭፈራዎችና ባህላዊ ክዋኔዎች የሚከሄዱበት መሆኑ ይታወቃል፡፡

ከኤ ኤም ኤን ኤፍ ኤም 96.3 ሬዲዮ ጋር ቆይታ ያደረገው የፊልም ዳይሬክተር፣ ደራሲ፣ ሙዚቀኛና ድምጻዊ ኤሊያስ ክፍሉ፣ ኢሬቻ ከተለያዩ አከባቢዎች የተወጣጡ ባህላዊ ትውፊቶችና እሴቶች የሚታዩበት መደረክ መሆኑን በማንሳት የኢሬቻ በዓልን ባህልና እሴት ለትውለድ ለማስተላለፍ ትልቅ አቅም አለው ብሏል፡፡

በተለይም የኤሬቻን በዓል ልክ እንደ ገዳ ስርዓት በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ድርጅት(በዩኔስኮ) ለማስመዝገብ ለተያዘው ጥረት፣ እሴቶቹን አጉልቶ ለዓለም ማሳየት እንደሚገባም ጠቁሟል፡፡

ለዚህ ደግሞ ኪነ ጥበብ ትልቅ ድርሻ አላት ያለው ባለሙያው፣ እስካሁን በኢሬቻ ዙሪያ ከሙዚቃ ክሊፖች እና ጥቂት ቀረጻዎች ቢኖሩም፣ በሚፈለገው ልክ ባህሉን አንጻባርቀናል የሚል እምነት እንደሌለው ተናግሯል፡፡

የፊልም ዳይሬክተር፣ ደራሲ፣ ሙዚቀኛና ድምጻዊ ኤሊያስ ክፍሉ፣ በግሉ ገዳ ሚሊባ ሀንገ ገዳ ሚልባ የሚል የኦሮሞን ባህል በጥቂቱ የሚያሳይ ዶክመንተሪ መስራቱን አስታውሶ፣ በቀጣይ የኢሬቻ በዓል እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ባህልና እሴትን የበለጠ አውጥቶ ማሳየት ብሎም ይህን ቱባ ባህል ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ገልጿል፡፡

ለዚህ ደግሞ የኪነ ጥብብ ባለሙያው መንግስትና ሀብረተሰቡ በጋራ መስራት እንዳለበትም አክሎ ተናግሯል፡፡

በረውዳ ሸምሱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review