የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለ2018 ኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለ2018 ኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈ

AMN – መስከረም 23/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለ2018 ኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል፡፡

የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት በመልካም ምኞት መግለጫው፤ ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መኖሪያ የብዝሀ ሃይማኖቶች ማህደር፣ የአብሮነት እና የመቻቻል አብነት የሆነች የብዝሀ ጸጋ ምድር ናት ሲል ገልጿል።

17 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በውስጡ አቅፎ የያዘው የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት፤ የሁሉም ህዝቦች ባህሎች እኩል መሆናቸውን ስለሚያምን ህዝባዊ እና ሀይማኖታዊ በዓሎችን በተመለከተ የመልካም ምኞት መግለጫዎች ማውጣትን ጨምሮ የሚጠበቅበትን ትብብር ሲያደርግ መቆየቱንና፤ ለወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ኢሬቻ በርካታ ባህላዊ እሴቶችን በማካተት የሚከበር በዓል ሲሆን፤ የእርቅና የይቅርታ፣ የአንድነትና የመቻቻል፤ የፍቅርና የመከባበር የተስፋና የመልካም ምኞት፣ የሠላምና የመረጋጋት እሴቶችን በውስጡ አቅፎ የያዘ መሆኑንም ምክር ቤቱ አስታውቋል።

በመሆኑም ምክር ቤቱ ለመላው የኦሮሞ ህዝብና ኢሬቻን የሚታደሙ ሁሉ እንኳን ለ2018 የኢሬቻ በአል አደረሳችሁ ሲል መልካም ምኞቱን ገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review