የምክር ቤቶቹ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ሰኞ ይካሔዳል

You are currently viewing የምክር ቤቶቹ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ሰኞ ይካሔዳል

AMN- መስከረም 23/2018 ዓ.ም

6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ሰኞ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሔዳል።

በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 58 ንዑስ አንቀፅ (2) እና በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 24 ንዑስ አንቀፅ (1) መሠረት የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንድ ዓመት የስራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑ ተደንግጓል፡፡

እንዲሁም በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 71 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽኑን ምክር ቤት ዓመታዊ የጋራ ስብሰባ እንደሚከፍት ተገልጿል፡፡

በዚሁ መሰረት የ6ኛው ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የተጠናቀቀ ሲሆን፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓትም የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት በተገኙበት ሰኞ መስከረም 26 ከቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ምክር ቤቱ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል በላከው መረጃ ገልጿል፡፡

በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ለሁለቱ የፌደራል መንግሥት ምክር ቤቶች (የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት) ዓመታዊ ስራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌደራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡

የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደሚገኙ የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ሙያዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ጸሃፊ ንጉሴ መሸሻ ( ዶ/ር) ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል በላከዉ መረጃ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review