ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ በሰው ሀብት ልማት ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ በሰው ሀብት ልማት ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ

AMN መስከረም 23/2018

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ በሰው ሀብት ልማት ዘርፍ ያላቸውን የጋራ ትብብር የበለጠ ለማጎልበት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አስታወቁ።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ የሰው ሀብት ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ማምታ ሙርቲ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ እና ምክትል ፕሬዝዳንቷ በውይይታቸው ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ በሰው ሀብት ልማት ያላቸውን አጋርነት ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በውይይቱ ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ ኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ፣ የእናቶች እና ህጻናት ሞት በመቀነስ እና የሴፍቲኔት ፕሮግራምን ተደራሽነት በማስፋት ያከናወነቻቸውን ስራ አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።

የዓለም ባንክ ሴፍቲኔት ፕሮግራም፣ ትምህርት፣ ክህሎት ልማት እና ጤናን ጨምሮ የኢትዮጵያ የሰው ሀብት ልማት እንዲሻሻል ለሚያግዙ ፕሮጀክቶች እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የዓለም ባንክ የሰው ሀብት ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ማምታ ሙርቲ ከውይይቱ በተጨማሪ በሃዋሳ ከተማ ጉብኝት አድርገዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቷ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የልማት አጋሮች የጤና ድጋፍ ማዕቀፍ (Health Compact) እና ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን ለማሳደግ የሚያግዙ ስራዎችን ጨምሮ ለኢትዮጵያ የሰው ሀብት ልማት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ማረጋገጣቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አስታውቋል።

የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት በተያዘው ሳምንት በአዲስ አበባ በኢትዮጵያ መንግስት እና የዓለም ባንክ ትብብር በተካሄደው የኢትዮጵያ የሰው ሀብት ልማት ፎረም ላይ መሳተፋቸው ይታወቃል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review