የ2018 የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል አከባበር አባ ገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች ወደ መልካ ከመሄዳቸው በፊት በባህሉ መሰረት አባ ገዳዎች በምርቃት ስነ- ስርዓት በዓሉን አስጀምረዋል፡፡
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበር ሲሆን፤ የሆረ ፊንፊኔ የሚከበርባት አዲስ አበባ ከተማ ከዋዜማ ጀምሮ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ደምቃለች።
መዲናዋ በዋዜማው በአምስቱም የመግቢያ በሮች በዓሉን ለመታደም የመጡ እንግዶችን በኢትዮጵያዊ እንግዳ አቀባበል ባህል በተለያዩ አካባቢዎች የተቀበለች ሲሆን፣ በምሽት ድባቡም የኢሬቻን በዓል የሚገልፅ የድሮን ትርኢት መቅረቡ ይታወሳል።
አባ ገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎችም በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ በማቅናት ላይ ይገኛሉ፡፡
በሔለን ተስፋዬ