ፈጣሪ ሆይ በትከሻህ ተሸከመን
ይህ በዓል የስኬት ይሁን
ገዳችን የሰላም ገዳ ይሁን
ይህ ጉባዬ የሰላም ይሁንልን
ኢሬቻ የሰላም ኢሬቻ የእውነት ነው
አንድነት የሰላም አንድነት ነው
ሰምምነቱ የሰላም ስምምነት ነው
ኢሬቻ የሰላም ይሁን
ፀደይ እጩ ነው እጩውን አሳካላት
ኢሬቻ ሰላም ነው፤ በሰላም አውለህ በሰላም አስገባን
ከመልካም ጋር አውለን
ከሰላም ቤት የመጣነው በሰላም ቀዬ አስገባን
ሰው ሰላም ይሁን
ከብቶች ሰላም ይሁኑ
አገራችንን ሰላም አድርግልን
ከክፉ ጦርነት ሰውረን
የተጣላን አስታርቅልን
ቀዬአችን አማን ይሁን
ከክፉ ጠብቀን
ደግ ደጉን አምጣልን
ኢትዮጵያን ሰላም አድርጋት
አካባቢውን ሰላም አድርግ
ከሰላምና እውነት ጋር አውለን
ዓመቱን የሰላም ይሁን
ዘመኑ የእድገት ይሁን
በ- መልካሙ አበበ