መዲናዋ ለአደባባይ ክብረ በዓላት፣ ለበዓሉ ታዳሚያንና ከመላዉ ዓለም ለሚመጡ ቱሪስቶች ተጨማሪ ድምቀት እና ምቾት መሆኗን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ አከባበር ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እጅግ በደመቀና ባማረ ሁኔታ መጠናቀቁን ገልፀዋል።
የሆረ ፊንፊኔ እሬቻ ክብረ በዓል የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የተለያዩ አገራት ጎብኚዎች፣ የባህልና ታሪክ ተመራማሪዎች በታደሙበት በልዩ ሁኔታ ደምቆ ተጠናቅቋል ብለዋል።

በኮሪደር እና በወንዝ ዳርቻዎች ልማት ያማረችዉ አዲስ አበባ ለአደባባይ ክብረ በዓላት፣ ለበዓሉ ታዳሚያንና ከመላዉ ዓለም ለሚመጡ ቱሪስቶች ተጨማሪ ድምቀት እና ምቾት መሆኗን ገልፀዋል።
በዓሉ እጅግ ባማረ፣ ደማቅ በሆነ መልኩ እሴቱንና ትውፊቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት ሁሉ ፣ በተለይም ለከተማዋ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡