‎የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል እሴቱን ጠብቆ በስኬት መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለፀ

You are currently viewing ‎የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል እሴቱን ጠብቆ በስኬት መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለፀ

‎AMN – መስከረም 24/2018 ዓ.ም

የገዳ ስርዓት አካል የሆነው የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል እሴቱን ጠብቆ በስኬት መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል፡፡

በርካታ ታዳሚዎች፣ ልዩ ልዩ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የውጭ ሀገር ዜጎችና ቱሪስቶች የታደሙበት “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የተከበረው የዘንድሮ የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በደማቅ ስነ-ስርዓት በስኬትና እሴቱን በጠበቀ ሁኔታ መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

በያዝነው አዲስ ዓመት በርካታ ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ያከበራቸው ኃይማኖታዊና ሕዝባዊ በዓላት ፍፁም በስኬት ተከብረው መጠናቀቃቸውን የገለፀው ፖሊስ፤ የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ በድምቀት ተከብሯል ብሏል፡፡

ለዚህ ስኬት አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ፎሌዎች፣ የከተማው ነዋሪ እንዲሁም በየእርከኑ የሚገኙ የአስተዳደር አካላት ላደረጉት አስተዋፅኦ እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታና የደህንነት ተቋማት አመራሮችና አባላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በፀጥታና ደህንነት ተቋማት ስም ምስጋናውን ማቅረቡን ለኤ አም ኤን በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ መምሪያው አያይዞ እንደገለፀው፣ በነገው እለት በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የሆረ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ተቋማት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ተግባር የገቡ ስለሆነ ህዝቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review