በአፋን ኦሮሞ ከተከታታይ የሬድዮ ድራማ ውስጥ “አባ ጃንቦ” በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል።
ለ20 ዓመታት በተከታታይ ለአድማጭ ሲደርስ እንደነበር የሚጠቀሰው አባ ጃንቦ፣ በዚህ ተከታታይ ድራማ ውስጥ ከተሳተፉ እውቅ ተዋንያን የኪነ ጥበብ ባለሙየዎች መካከል አንዷ አርቲስት አበበች አጀማ ናት።
አርቲስት አበበች ፣ በሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ለማክበር ከተገኙ ታዋቂ የኪነ-ጥበብ ሰዎች መካከል አንዷ ናት።
በዓሉ ከተሰራው የመሰረተ ልማት ጋር ተዳምሮ ለከተማዋ ልዩ ውበት ከማላበሱ በተጨማሪ ፣ በዓሉን በአንድነት፣ በፍቅር እና በደስታ ማክበራቸውን ተናግራለች።
ኢሬቻ ማለት ውሀውን፣ ቄጠማውን እና የተፈጥሮ ሀብትን የፈጠረ አምላክን ከክረምትና ከጭጋጋማው ወቅት ወደ ብራ ስላሸጋገረን የምናመሰግንበት ቀን ነው ብላለች።
የኢሬቻን በዓል ከኦሮሞ ተወላጆች በተጨማሪ የተለያዩ ብሄረሰቦች በድምቀት ያከበሩበት ጊዜ መሆኑ አስደሳች ነው ብላለች።
የኢሬቻ በዓል አከባበር ከአመት አመት ውበቱ እያማረ እና እየፈካ እንደሚገኝ ምልከታዋን አጋርታለች።
በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማትን ስትመለከት ውጭ አገር እንደሚመስላት ገልፃ፣ ከተማዋ እንደ ስሟ አዲስ መሆኗ አስደስቶኛል ብላለች።
በሔለን ተስፋዬ