አርሰናል የሊጉ መሪ የሆነበትን ድል ሲያስመዘግብ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ድል ተመልሷል

You are currently viewing አርሰናል የሊጉ መሪ የሆነበትን ድል ሲያስመዘግብ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ድል ተመልሷል

AMN-መስከረም 24/2018 ዓ.ም

ዌስትሃም ዩናይትድን በሜዳው ኤምሬትስ ያስተናገደው አርሰናል 2ለ0 አሸንፏል።

የመድፈኞቹን ግብ ዴክለን ራይስ በጨዋታ እንዲሁም ቡካዮ ሳካ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፈዋል።

200ኛ የሊግ ጨዋታውን ያደረገው ሳካ 100ኛ የግብ ተሳትፎው ሆኗል። የ24 ዓመቱ እንግሊዛዊ 55 ግብ ሲያስቆጥር 45 ግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል። አርሰናል በሜዳው ከሁለት የውድድር ዓመት ሽንፈት በኋላ ዌስትሃምን መርታት ችሏል። በጨዋታው አምበሉ ማርቲን ኦዴጋርድ በመጀመሪያው አጋማሽ ጉዳት ገጥሞት ተቀይሮ ወጥቷል።

በሰባት ጨዋታ 16 ነጥብ የሰበሰበው አርሰናል የሊጉ መሪ ሆኗል። በኦልድትራፎርድ ሰንደርላንድን ያስተናገደው ማንችስተር ዩናይትድም 2ለ0 አሸንፏል።

ሜሰን ማውንት እና ቤንጃሚን ሼሽኮ ያስቆጠሯቸው ግቦች ዩናይትድን ወደ ድል መልሰዋል። ለዩናይትድ በኦልድትራፎርድ ያሳካው ሦስተኛ ተከታታይ ድሉ ሆኖም ተመዝግቧል።

ቀያይ ሰይጣናቱ በ10 ነጥብ ወደ ስምንተኛ ደረጃ ከፍ ብለዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review