የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት ከተማዋን ከምቹ የዓለም ከተሞች ተርታ እንደሚያሰልፍ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ምሁራን ገለጹ

You are currently viewing የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት ከተማዋን ከምቹ የዓለም ከተሞች ተርታ እንደሚያሰልፍ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ምሁራን ገለጹ

AMN- መስከረም 24/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት ከተማዋን ምቹ ከሆኑ የዓለም ከተሞች ተርታ የሚያሰልፍ ነው ሲሉ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ምሁራን ገልጸዋል።

ከተለያዩ ሀገራት የመጡት የታሪክ፣ አርኪዮሎጂ እና የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪዎች፣ በከተማዋ እየተከናወነ ያለውን የልማት ስራ ጎበኝተዋል።

ተመራማሪዎቹ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው ጥናታዊ የውይይት መድረክ ላይ ለመሳተፍ የመጡ ሲሆን፣ አድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለውን የወንዝ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ጎብኝተዋል።

በአዲስ አበባ የተመለከቱት የልማት ስራ እንዳስገረማቸው የገለጹት ተመራማሪዎቹ፣ ልማቱ ከተማዋን ከምቹ የዓለም ከተሞች ተርታ የሚያሰልፋት ነው ብለዋል።

የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከልና ተፈጥሮን ከመጠበቅ አንፃርም እየተከናወነ ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት አንስተዋል።

ለተመራማሪዎቹ ሰለወንዝ ዳርቻ ልማቱ ያብራሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ፣ በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የልማት ስራ ሀገሪቱን ለዓለም በመልካም የሚያስተዋውቅ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ጎብኚዎቹም ስለ ከተማዋ የተሻለ ግንዛቤ እንዲይዙ መደረጉንም ገልጸዋል።

በአሰግድ ኪዳነማሪያም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review