አዲስ አበባ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ኩነቶችን ጨምሮ የአደባባይ ክብረ በአላትንና ሌሎች ኩነቶችን በብቃት የማስተናገድ ችሎታዋ እያደገ መምጣቱና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚቀመጥ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing አዲስ አበባ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ኩነቶችን ጨምሮ የአደባባይ ክብረ በአላትንና ሌሎች ኩነቶችን በብቃት የማስተናገድ ችሎታዋ እያደገ መምጣቱና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚቀመጥ መሆኑ ተገለጸ

AMN መስከረም 24/2018

አዲስ አበባ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ኩነቶችን ጨምሮ የአደባባይ ክብረ በአላትንና ሌሎች ኩነቶችን በብቃት የማስተናገድ ችሎታዋ እያደገ መምጣቱና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚቀመጥ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር አዲስ አበባ የአደባባይ በአሎችንና ትላልቅ ኩነቶችን የማስተናገድ አቅሟ እያደገ የመጣ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚቀመጥ መሆኑን ገምግሟል፡፡

በአዲስ አበባ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ኩነቶች ፣ የአደባባይ ክብረ በአሎች በተከታታይ ከፍ ባለ ስነ-ስርአት ፣ ደማቅ ፣ ዉብ ፣ ፍፁም ሰላማዊ እና ስኬታማ ሆነዉ መከናወናቸዉ የከተማዋን የትኛዉንም ኩነት በብቃት የማስተናገድ ችሎታዋ እያደገ መምጣቱን ያሳያል ።

ለአብነትም በከተማዋ የተካሄዱት የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ፣ የአፍሪካ ካረቢያን መሪዎች ጉባኤ፣ የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ህዝባዊ ሰልፍ ፣ የመስቀል ደመራ ፣ ኢሬቻን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ በነቂስ ወደ አደባባይ ወጥቶ ያለ አንዳች ኮሽታ ፣ አንድም መሰረተ ልማት ሳይበላሽ ፣ በታላቅ ስነስርአት ፣ ደማቅና ዉብ ሆነዉ እንዲስተናገዱ ማስቻል ትልቅ ትርጉም የሚሰጠዉ ነው ።

ለዚህም በከተማዉ የተሰሩ የልማት ስራዎችና መሰረተ ልማቶች ወደ አደባባይ ለሚተመዉ ነዋሪና ጎብኚ የሚፈጥሩት ተጨማሪ ዉበት እና ምቾት አዲስ አበባን የስህበት ማዕከል ማድረጉን የተገመገመ ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታ ኢኮኖሚዉን ያነቃቃና የአለም አቀፍና የአገር ዉስጥ ጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንም አንስቷል።

በዋናነት የከተማው ህዝብ በሀላፊነት ስሜት ፣ በሃይማኖት ፣ በብሄር ፣ በፓለቲካ አቋም ሳይለያይ ፣በወንድማማችነትና እህትማማችነት መንፈስ ከመንግስት ጋር በሁሉም መስክ መስራቱ ፣ የሆቴልና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፣ በከፍተኛ ዝግጅት አገልግሎት ማቅረባቸዉ ፣ እንዲሁም ምርቶቻቸዉን በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ገበያ በማቅረብ የምርት እጥረት እና የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ፣ የግብርና ምርት አቅራቢዎች ፣ የፓለቲካ አመራሩ እና የፀጥታ ተቋማት በቅንጅት የተሰራ ስራ ዉጤት ስለሆነ ለሁሉም አካላት ከልብ ምስጋና ይገባቸዋል ።

የከተማው ከፍተኛ አመራር በመተባበርና በመደጋገፍ የተመዘገበው ስኬት ለኢትዮዽያ ትልቅ የአብሮነትና የማንሰራራት መሰረት ስለሆነ ይበልጡን አጠናክረን እናስቀጥላለን ማለቱን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review