ኮሚሽኑ ከስቶክሆልም መድረክ ተሳታፊዎች አጀንዳዎችን ተረከበ

You are currently viewing ኮሚሽኑ ከስቶክሆልም መድረክ ተሳታፊዎች አጀንዳዎችን ተረከበ

AMN መስከረም 24/2018 ዓ.ም

ወደ ሲዊዲን ያቀናው የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ልዑክ በሲዊዲን፣ በኖርዲክ ሀገራት እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተለዩ አጀንዳዎችን ተረክቧል፡፡

ኮሚሽኑ በሲዊዲን፣ በኖርዲክ ሀገራት እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ያሰባሰበበትና የሀገራዊ ምክክር ተሳታፊዎችን ያስመረጠበት መድረክ በስዊዲን ስቶክሆልም መስከረም 24/2018 ዓ.ም አካሂዷል፡፡

በመድረኩ በሲዊዲን፣ በኖርዲክ ሀገራት እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የወከሉ ተሳታፊዎች አጀንዳዎቻቸውን በተለያዩ ቡድኖች በማጠናቀርና በማደራጀት ለኮሚሽኑ አስረክበዋል፡፡

በመድረኩ የተሳተፉ የዳያስፖራ አባላት በሲዊዲን፣ በኖርዲክ ሀገራት እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ወክለው በኢትዮጵያ በቅርቡ በሚካሄደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ወኪሎችንም መርጠዋል::

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገ/ስላሴ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር በሲዊዲን፣ በኖርዲክ ሀገራት እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በምክክሩ ላደረጉት ንቁ ተሳትፎ በኮሚሽኑ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በኮሚሽኑ የአሠራር ሥርዓት መሠረት በዚህ መድረክ የተሰበሰቡ አጀንዳዎችም ከሌሎች አጀንዳዎች ጋር በኮሚሽኑ ምክር ቤት ተቀርፀው ለሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ግብዓት እንዲሆኑ የሚደረግ መሆኑን ኮሚሽኑ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review