የሆረ ሃርሰዴ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ መከበሩን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገልጸዋል፡፡
በአሉ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ በድምቀትና በስኬት እንዲከበር አስተዋጽኦ ላደረጉ አካለትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲ የኦሮሞ ህዝብ ከወንድም ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በመሆን በሆረ ሃርሰዴ በአንድነት፤ በወንድማማችንትና በአብሮት ተገናኝቶ በአሉን በስኬት በማክበሩን ገልጸዋል፡፡
አዲሱ አመት ለኦሮሞ ህዝብም ሆነ ለመላዉ የሃገሪቱ ህዝቦች የማንሰራራት ዘመን ነዉ ያሉት ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ አዲሱን አመት አንድነትን በማወጅ ጀምረናል ፤ ለዚህም ለመላዉ ህዝብ ምስጋና ይገባል ብለዋል፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር : የጸጥታ ተቋማትን እና መላዉ የክልሉን ህዝብ ጨምሮ የሆረ ሃርሰዴ የኢሬቻ በአል በስኬትና በድምቀት እንዲከበር የጎላ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትንም አመስግነዋል፡:
በወንድማገኝ አሰፋ