የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል የብሄር ብሄረሰቦች አብሮነትና ወንድማማችነት ጎልቶ የታየበት መሆኑን በበአሉ ላይ የታደሙት አባገዳ ለሜቻ ለማ ገለጹ፡፡
አባገዳ ለሜቻ ለማ የሆረ ፊንፊኔ እና የሆረ ሃርሰዴን የኢሬቻ በዓል አስመልክቶ ለኤ.ኤም.ኤን እንደተናገሩት በአሉ በስኬትና በድምቀት መከበሩ የብሄር ብሄረሰቦች አብሮነትና ወንድማማችነት እየተጠናከረ ስለመምጣቱ ማሳያ ነዉ ብለዋል፡፡
የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በአዲስ አበባና በቢሾፍቱ በተከናወነዉ የኢሬቻ በአል አከባበር ሥነ ሥርዓት ላይ በመታደም አብሮነታቸዉን አሳይተዋል፡፡

የበአሉ ታዳሚዎች በአሉን ለማክበር በሚንቀሳሰቁበት ወቅትም በተለያዩ ከተሞች በወንድማማችን መንፈስ ተቀብለዉ አስተናግደዋል፡፡
ይህም ኢትዮጵያ የህዝቦችን ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክሩ ባሕላዊና ማህበራዊ እሴቶች እንዳላት የሚያመላክት ነዉ ብለዋል፡፡
እነዚህ ባህላዊ እሴቶች እንደ አንድ ማኅበረሰብ ለረጅም ዘመናት ያለምንም ልዩነት አብረን እንድንኖር አድርገውናል፤ ነገም ተጠናክረዉ ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በ ፍሬሕይወት ብርሃኑ