ከጳጉሜን ወር 2017 ዓ.ም ጀምረው እስከ ዛሬ ድረስ ሕዝብ በስፋት የተሳተፈባቸው በኢትዮጵያ የተካሄዱ ታላላቅ ሁነቶች በስኬት መጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ ገልጿል፡፡

በመረጃው፤ ለሁነቶቹ በስኬት መከወን ከፍተኛ ድርሻ ለተወጡ አካላት ሁሉ ፌደራል ፖሊስ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።
ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር ከጳጉሜን ወር ጀምሮ በሀገራችን የተካሄዱና የተከበሩ ታላላቅ ሁነቶች በስኬት እንዲጠናቀቁ ለማድረግ ኅብረተሰቡ ያሳየውን ከፍተኛ ትብብር የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡