የአማራ ክልል ፖሊስ አዲስ የለውጥ ጉዞ ስኬት አንዱ የድል ምልክት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ

You are currently viewing የአማራ ክልል ፖሊስ አዲስ የለውጥ ጉዞ ስኬት አንዱ የድል ምልክት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ

AMN – መስከረም 25/2018 ዓ.ም

የአማራ ክልል ፖሊስ አዲስ የለውጥ ጉዞ ስኬት አንዱ የድል ምልክት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ የአማራ ክልል ፖሊስ የማይናወጥ የህዝብ አገልጋይና የህግ አስከባሪ ተቋም የሚያደርገውን የለውጥ ጉዞ ጀምሯል፡፡

ዛሬ ተቋሙ የጀመረውን ሪፎርም፣ የዲጂታላይዜሽን ሥራና አዲሱን የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ መመረቃቸውንም ገልጸዋል።

የአማራ ክልል በሁለት ግንባር፣ ከጥፋት ኃይሎች እና ከድህነት ጋር ተዋግቶ ሁለቱንም በማሸነፍ ምዕራፍ ላይ ይገኛል ብለዋል።

ክልሉ ደረጃ በደረጃ ሁለቱንም በመርታት ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የአማራ ክልል ፖሊስ አዲስ የለውጥ ጉዞ ስኬትም አንዱ የድል ምልክት ነው ብለዋል።

የክልሉ ፖሊስ የወንጀል መከላከልና የምርመራ አቅሙን ለማላቅ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተደራጀ፣ በሙያዊ ታማኝነትና በላቀ የህዝብ አገልጋይነት እሳቤ የተቃኘ ዘመናዊ አሠራር እየዘረጋ ይገኛል።

የተቋሙ የለውጥ ጉዞ መዳረሻ ከህንፃና ከዲጅታል መሠረተ ልማት የተሻገረ፣ ህዝብን ከጥፋት ኃይሎች የመጠበቅ እምነትን መገንባት፣ ህግና ፍትሕን ማረጋገጥ እና ዘላቂ ሰላምን ማስፈን ነው።

ፖሊስ ለሕዝቡ አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት ከፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዳ፣ በሃይማኖት ጣልቃ የማይገባ፣ ከሌብነት የጸዳ እና ጎጠኝነትን የሚጸየፍ ሊሆን ይገባዋል ብለዋ።

ሪፎርሙም እነዚህን በማሳካት ደማቅ ታሪክ የሚፅፍ የፖሊስ ኃይል ማፍራት ነው፤ እንደሚሳካም ሙሉ ዕምነት አለኝ ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review