በስፔን ላሊጋ 8ኛ ሳምንት በራሞን ሳንቼዝ ፒዥዋን ስታዲያም ሲቪያን የገጠመው ባርሰሎና 4ለ1 ተሸንፏል።
የቀድሞ የባርሰሎና ተጫዋች አሌክሲስ ሳንቼዝ በፍፁም ቅጣት ምት ፣ ኢሳክ ሮሜሮ ፣ ጆሴ አንሄል ካርሞና እና አኮር አዳማስ የሲቪያን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

የባርሰሎናን ግብ ማርከስ ራሽፎርድ አስቆጥሯል። በጨዋታው ሮበርት ሌቫንዶቭስኪ ፍፁም ቅጣት ምት አምክኗል።
የካታሎኑ ክለብ በላሊጋው ሽንፈት ሲገጥመው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
የሀንሲ ፍሊኩ ቡድን በሳምንቱ አጋማሽ በቻምፒየንስ ሊጉም በፓሪሰን ዠርማ መሸነፉ ይታወሳል።
በሸዋንግዛው ግርማ