የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለፁ

You are currently viewing የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለፁ

AMN – መስከረም 26/2018 ዓ.ም

መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶችን ለመጠገን ተግባራዊ ያደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ውጤት እያስገኘ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ እያደረጉ በሚገኙት ንግግር፤ በአዲሱ ዓመት መባቻ የበርካታ ዓመት ቁጭት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቁ እና በመስከረም ወር መባቻ የከርሰ ምድር ሀብታችን የሆነው የተፈጥሮ ጋዝ መውጣቱ የኢትዮጵያ እድገት መልህቅ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶችን ለመጠገን ተግባራዊ ያደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ውጤት እያስገኘ እንደሚገኝም ማመላከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከነጠላ ወደ ብዝሃነት የኢኮኖሚ ልማት በመሸጋገር እየተከናወኑ ባሉ ስራዎች የኢትዮጵያ ኤክስፖርት እያደገ እና ኢኮኖሚው ተጨባጭ ለውጥ እያሳየ ይገኛል ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review