የተማሪዎች ምገባ ኘሮግራም ከዓለም አቀፍ ተቋማት እውቅና የተሰጠው መሆኑን ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለፁ፡፡
በትውልዶች ውስጥ የሚስተዋለው የእሴት መሸርሸር ዋነኛ መነሻ የትምህርት ጥራት ችግር ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ፤ ይህንን ሳንካ ለመቅረፍ ባለፈው አመት በትምህርት ጥራት ላይ በትኩረት ተሰርቷል ብለዋል፡፡
መንግስት የትምህርት እና ስልጠና ፖሊሲ ቀርፆ ተግባራዊ አድርጓል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ትምህርት ለትውልድ በሚል መሪ ቃል ማህበረሰቡን በማንቀሳቀስ በተሠራው ስራ የትምህርት ተደራሽነትን ማረጋገጥ ተችሏል ነው ያሉት፡፡
የተማሪዎች ምገባ ኘሮግራም ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ ማስቻሉን ገልፀው፤ ይህ ጉልህ ተግባር ከዓለም አቀፍ ተቋማት እውቅና የተሰጠው ነው ብለዋል፡፡
በ-በረከት ጌታቸው