7ኛዉ ሀገር አቀፍ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተአማኒ እንዲሆን መንግስት በኃላፊነት ይሰራል ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ መላው የሀገራችን ህዝብ ኢትዮጵያ ያቀደቻቸውን ግዙፍ የለውጥ እርምጃዎች አበርትቶ እንዲደግፍና በትጋት እንዲሳተፍ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የልማት እና የእድገት አጋሮችም ከኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ጎን በመቆም የዚህ ስኬት ሁነኛ አጋዥ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በ- ታምራት ቢሻው