የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በተወሰደው እርምጃ የኑሮ ውድነትን መቀነስ መቻሉን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አመላከቱ

You are currently viewing የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በተወሰደው እርምጃ የኑሮ ውድነትን መቀነስ መቻሉን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አመላከቱ

AMN- መስከረም 26/2018 ዓ.ም

የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በተወሰደው ተከታታይ እርምጃዎች የኑሮ ውድነትን መቀነስ መቻሉን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አመላክተዋል፡፡

በሁለቱ ምክር ቤቶች መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንቱ፣ የኑሮ ጫናን እና የዋጋ ንረትን ለመቀነስ በተሰራው ሥራ ውጤት መመዝገቡን ገልፀዋል።

በተወሰዱ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ከተመዘገበው 19 ነጥብ 9 በመቶ የዋጋ ንረት በ2017 ዓ.ም ተመሳሳይ ወር ላይ ወደ 13 ነጥብ 9 በመቶ ዝቅ ብሎ መመዝገቡን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

መንግስት የመንግስት ሰራተኛውን የኑሮ ጫና ለመቀነስ የደሞዝ ማሻሻያ ማድረጉን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ በዚህም ከዚህ በፊት ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ 4 ሺህ 760 ከነበረበት ወደ ብር 6 ሺህ እንዲያድግ መደረጉን ገልጸዋል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review