ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጪ ንግድ 8.3 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን ‎ኘሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለፁ

You are currently viewing ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጪ ንግድ 8.3 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን ‎ኘሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለፁ

‎AMN – መስከረም 26/2018 ዓ.ም

‎ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጪ ንግድ 8.3 ቢሊዮን ዶላር አግኝታለች ሲሉ ኘሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገልፀዋል።

‎ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ታሪካዊ እጥፋት በማስመዝገብ ከወጪ ንግድ 8.3 ቢሊዮን ዶላር አጊንታለች ያሉት ኘሬዝዳንቱ፣ ከ2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር 115.8 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን አመላክተዋል።

‎በሲሚንቶ ምርት በ2016 በጀት ዓመት 7.5 ሚሊዮን ቶን መገኘቱንን እና ይህም በ2017 በጀት አመት 9.1 ሚሊዮን ቶን መገኘቱን ተናግረዋል።

‎ከ150 በላይ አለም አቀፍ ኮንፈረንሶች በሃገሪቱ መካሄዳቸውን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ የዲጅታል ኢኮኖሚ አመላካቾች በከፍተኛ ሁኔታ እድገት አሳይተዋል፡፡

‎የባንክ ብድር የመስጠት አቅም በማደጉ 822.8 ቢሊዮን ብር ብድር መለቀቁን እና ከዚህ ውስጥ 77 በመቶ ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

‎በ- ሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review