የአዲስ አበባ ከተማ በዓለም ለኑሮ ምቹ ከሆኑ ከተሞች ተርታ መመደብ የምትችል መሆንዋን የውጭ ሀገራት ሙሁራን ተናገሩ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ በዓለም ለኑሮ ምቹ ከሆኑ ከተሞች ተርታ መመደብ የምትችል መሆንዋን የውጭ ሀገራት ሙሁራን ተናገሩ

AMN መስከረም – 27/2018 ዓ.ም

ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የታሪክ፣ የአርኪኦሎጂስቶችና የማህበራዊ ሳይንስ ሙሁራኑ ለኤ አም ኤን እንደገለጹት፣ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ባለው የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራ መገረማቸውንና ከተማዋንም ከምቹ የዓለም ከተሞች ተርታ የሚያሰልፋት ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡

ከዩናይትድ ኪንግደም የመጡት ምሁር ዴቪድ ፊሊፕስ፣ ወደ አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2007 ላይ መጥተው እንደነበር አስታውሰው፣ በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ የመጣውን ለወጥ አድንቀዋል፡፡

ከከተማዋ ንጽህና ጋር በተያያዘ ከአሁን ቀደም የማይመቹ ሁኔታዎች መኖራቸዉ፤ በየቦታው ቆሻሻ እና ደስ የማይል ሽታ እንደነበር ያነሳሉ፡፡

አሁን ላይ ግን ከተማዋ በብዙና በሚደንቅ ሁኔታ ተለዉጣለች፤ በተለይ በከተማዋ እየተከናወነ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ልማት ስመለከት በጣም ተገርሜያለሁ ብለዋል፡፡

ከእስራኤል የመጡት ሌላኛው ምሁር ጌዲዮን ቦሃክ በበኩላቸው፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የወንዝ ዳርቻ የልማት ስራዎችን ስመለከት በጣም የሚደንቁ ናቸው ብለዋል፡፡

ያላለቁ የወንዝ ዳርቻ ስራዎች ሲጠናቀቁ፣ ከተማዋ ይበልጥ የምታምርና የምትዋብ ትመስለኛለች ነው ያሉት ምሁሩ፡፡

በአሁኑ ሰዓት የአዲስ አበባ ከተማን ልማት በግልፅ ማየት ችያለሁ፡፡ ህፃን እያለሁ በንጉሱ ዘመን አዲስ አበባን የማየት እድል ገጥሞኝ ነበር የሚሉት ደግሞ ከዩናይትድ ኪንግደም የመጡት ምሁር ስታሊቪን ናቸው፡፡

በጥቂት አመታት ውስጥ በጣም ትልቅ ለውጥ አይቻለሁ፤ እንዲህ አይነት ነገር መስራት ቀላል አይደለም፤ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፤ ለዚህ ደግሞ ብልህነትን ይጠይቃል ብለዋል ሙሁሩ፡፡

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review