የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ለእለቱ የተያዙ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ውይይቱን ማካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ቃለጉባዔውን መርምሮ አጽድቋል።

ጉባኤው ዉይይቱ የቀጠለ ሲሆን በጉባኤው ያጸደቃቸውን ሌሎች አጀንዳዎች በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፍባቸው ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።