8ኛው የወጣት የስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፍሬዎች ፌስቲቫል የማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing 8ኛው የወጣት የስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፍሬዎች ፌስቲቫል የማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ነው

AMN- መስከረም 27/2018 ዓ.ም

8ኛው የወጣት የስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፍሬዎች ፌስቲቫል የማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ በአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት እየተካሄደ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

“በለውጡ የተለወጠ ወጣት” በሚል መሪ ሃሳብ ከሁሉም የመዲናዋ ክፍለ ከተሞች የስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የተውጣጡ ወጣቶች ተሰጥኦዋቸውን አውጥተው ለሃገር ይተርፉ ዘንድ በተለያዩ የኪነጥበብ ዘርፎች ሲወዳደሩ ቆይተዋል።

ተተኪ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ለማፍራት ያለመው ውድድሩ፣ ከወረዳ ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፣ በዛሬው እለትም በክፍለ ከተሞች ደረጃ የማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ነው።

መዲናዋ ባሏት 114 የወጣት የስብዕና መገንቢያ ማዕከላት፣ ወጣቱ መክሊቱ በስብና ታግዞ ለሃገር የሚተርፍበትን ሁኔታ ለመፍጠር እየሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ገልጸዋል።

ወጣቱን በስልጠና እና የተለያዩ መንገዶች በአመለካከትና አስተሳሰብ በማነፅ በወጣቶች ተጠቃሚነት ላይ ሲሰራ መቆየቱንም ኃላፊው ጠቁመዋል።

የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላቱ ከሚሰጧቸው 18 አገልግሎቶች ውስጥ አንዱ ኪነጥበብ መሆኑም ተመላክቷል።

በ-መቅደስ ደምስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review