ተማሪዎችን በአካልና በአእምሮ ዝግጁ ንቁና ብቁ ማድረግ ዓላማ ያደረገ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

You are currently viewing ተማሪዎችን በአካልና በአእምሮ ዝግጁ ንቁና ብቁ ማድረግ ዓላማ ያደረገ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

AMN- መስከረም 27/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በትምህርት ቤቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አስጀምሯል።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴው ተማሪዎችን በአካልም በአእምሮም ዝግጁ በማድረግ ንቁ እና ብቁ ሆነው እንዲማሩ ማድረግን አላማ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

“ብቁና ንቁ ትውልድ እንፍጠር” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከናወነው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ በሳምንት ሁለት ጊዜ እንደሚካሄድም ተገልጿል።

በሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ መካከለኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተጀመረው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ እና የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አመራሮች፣ መምህራንና ተማሪዎች ተሳትፈዋል።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review