የሆረ ፊንፊኔ እና የሀረ አርሰዴ የኢሬቻ በዓል በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ካሜራ አይን

You are currently viewing የሆረ ፊንፊኔ እና የሀረ አርሰዴ የኢሬቻ በዓል በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ካሜራ አይን

AMN- መስከረም 27/2018 ዓ.ም

የዘንድሮው የሆረ ፊንፊኔ እና የሆረ ሃርሰዴ የኢሬቻ በአል አከባበር የበርካታ የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀንን ትኩረት በመሳብ ሰፊ ሽፋንን አግኝቷል።

የኦሮሞ ህዝብ የገዳ ስርአት መገለጫ የሆነው የኢሬቻ በአል አከባበር ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በአዲስ አበባ ሆረ ፊንፊኔ ፣ በቢሾፍቱ ሆረ አርሰዴ በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።

ቢቢሲ Selfies and singing as Ethiopians celebrate thanksgiving በሚል ርዕስ ባወጣው ዘገባ በኢሬቻ የተንጸባረቀውን ባህላዊ አልባሳት እንዲሁም ውበት እና ፋሽንን ትኩረት አድርጎ የፎቶ ዘገባን ለተከታዮቹ አድርሷል።

ባለፉት ቅርብ አመታት በክብረ በዓሉ ላይ የሚሳተፉ ወጣቶች ቁጥር መበርከት የኦሮሞ ባህልን የሚያንጸባርቁ አልባሳት በተለያየ ፋሽን እንዲሰሩ እና በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እንዲንጸባረቁ ማስቻሉን ዘገባው ጠቅሷል።

ክብረ በዓሉ በሀገረ ውስጥ የወንድማማችነት እና የህብረ ብሔራዊነት መገለጫ ከመሆን ተሻግሮ አለም አቀፍ ተሳታፊዎችን እና ጎብኝዎችን ቀልብ በመሳብ ላይ እንደሚገኘ ከፎቶው ጋር ተያይዞ የወጣው ዘገባ ያትታል።

ባለፈው አመት በተከበረዉ የኢሬቻ በአል ላይ የታደሙ አንድ የሰሜናዊ አየርላንድ ጎብኚ በዘንድሮው አመት ልጆቻቸውን ጭምር ይዘው መሳተፋቸውን ተናግረዋል፡፡

የምስጋና በዓል በሆነው ኢሬቻ የወጣቶች ጭፈራ እና በህብረቀለማት ያሸበረቁ አልባሳት ለበአሉ ተጨማሪ ድምቀት እንዳላበሱትም ቢቢሲ በዘገባው አክሏል።

በዳዊት በሪሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review