ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሀገራችን ኩራት ከሆነው የኢትዮዽያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር በጋራ በምንሰራባቸው ጉዳዮች ላይ ዛሬ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል ሲሉ ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሀገራችን ኩራት ከሆነው የኢትዮዽያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር በጋራ በምንሰራባቸው ጉዳዮች ላይ ዛሬ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል ሲሉ ገለጹ

AMN መስከረም 27/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የሀገራችን ኩራት ከሆነው የኢትዮዽያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር በጋራ በምንሰራባቸው ጉዳዮች ላይ ዛሬ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያውያንን ከዓለም ጋር ከሚያገናኛው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሳውን እና ማኔጅመንታቸውን የወንዝ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማትን ካስጎበኘናቸው በኋላ በተደራጀ እና በተቀናጀ መልክ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረምን ሲሆን፣ ስምምነቱ በዋናነት በከተማችን የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት የለሙ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን የማስተዋወቅ በዚህም የስቶክ ኦቨር ቱሪዝም ተጠቃሚነትን ማሳደግ፣ የከተማችን አዲስ መለያ የሆነውን new face of Africaን ማስተዋወቅ፣ የአቪየሽን ደህንነትን ማረጋገጥ፣ በተጨማሪም በከተማው የተለያዩ ማህበራዊና ሰው ተኮር ስራዎችን በጋራ መስራት ላይ ያተኮረ ነው ።

አየር መንገዱ በከተማችን በምንሰራቸው ሰው ተኮር የልማት ስራዎች እና በኮሪደር ልማት ላይ ለነበረዉ ድጋፍ ከልብ እያመሰገንን ፣ የከተማ አስተዳደራችን ለስምምነቶቹ ተፈፃሚነት ከኢትዮዽያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር ከከዚህ ቀደሙ በበለጠ ተቀራርቦ የሚሰራ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review